Wednesday, December 4, 2019

ሰልክ ውሀ ዉስጥ ሲገባ ማድረግ ያለብን 6 ነገሮች

በተለያዩ አጋጣሚዎች ስልክዎ ዉሀ ዉስጥ ሊገባ ይችላል። ይህ ሁኔታ ሲፈጠር ከመደናገጥ ይልቅ ቀላል የሆኑ አካሄዶችን በመከተል ስልክዎ እንዳይበላሽ ማድረግ ይችላሉ፡፡
ከሁሉም በፊት ስልክዎን በፍጥነት ከዉሀ ዉስጥ ማዉጣት ይኖርቦታል፡፡ ስልክዎ ዉሀ ዉስጥ በቆየ ቁጥር ዉሀ ወደ ስልክዎ ዋና ክፍሎች ዉስጥ የመግባት እድሉ ከፍተኛ ነዉ፡፡
🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥
ሊከተሉዎቸዉ የሚገቡ ጥንቃቄዎችን እንመልከት።
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
በፍጹም ሊያደርጉዎቸዉ የማይገቡ ነገሮች 👇👇👇👇

✔️ ስልክዎን እንዳያበሩት
✔️ ስልክዎ ላይ የሚገኙትን ቁልፎች አይንኩ
✔️ ስልክዎን አያወዛዉዙት ወይም ስልክዎ ከሌሎች ነገሮች ጋር አያጋጩት
✔️ የስልክዎን ዉስጠኛ ክፍሎች አይንቀሉ፡፡ [ስልክዎ የዉሀ ብልሽት አመላካች(Liquid Damage Indicator(LDI)) ተገጥሞለታል፣ የስልክዎን ዉስጠኛ ክፍሎች የሚከፍቱት
ከሆነ ይህ የዉሀ ብልሽት አመላካች አክቲቭ(Active) ይሆናል፡፡ ይህ ደግሞ ከስልኩ አምራች ድርጅት የሚሰጠዉን Warranty ያሳጣዎታል፡፡]
✔️ በትንፋሽዎ ዉሀዉን ለማድረቅ አይሞክሩ፣ ምክንያቱም ስልክዎ ላይ በሚተነፍሱበት ጊዜ ዉሀ ወደ ዉስጠኛዉ
የስልክዎ ክፍል ዉስጥ ሊገባ ስለሚችል ነዉ፡፡
✔️ ስልክዎን በማንኛዉም አይነት የሙቀት መሳሪያ ለማድረቅ አይሞክሩ፡፡
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖

ዉሀ ዉስጥ የገባን ስልክ ከብልሽት የሚከላከሉባቸዉ አካሄዶች 👇
🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥
1) ስልክዎን ከዉሀ ዉስጥ ሲያወጡት እየበራ ከሆነ ያጥፋት እና ቀጥ አድርገዉ ይያዙት፡፡
2) የስልክዎን ከቨር በመክፈት ባትሪ፣ ሲም ካርድ እና ሚሞሪ ካርዱን ያዉጡ፡፡
3) ደረቅ ጨርቅ ወይም ማድረቂያ በመጠቀም ስልክዎን
ያድርቁ፡፡ [ዉሀ ወደ ሌላ የስልክ ክፍሎች እንዳይተላለፍ ይጠንቀቁ፡፡]
4) በጐድጓዳ ሰሀን ላይ ያልተቀቀለ ሩዝ ይጨምሩ እና ስልክዎን ሩዝ ዉስጥ ይክተቱት፡፡ ሩዝ ዉሀን የመምጠጥ አቅሙ በጣም ከፍተኛ ስለሆነ አብዛኛዉን ጊዜ ስማርት ስልኮችን እና ታብሌቶችን ለማድረቅ ጥቅም ላይ ይዉላል፡፡
5) ስልክዎ በሩዝ ዉስጥ ለአንድ ወይም ሁለት ቀን እንዲቆይ ያድርጉ፡፡ በእነዚህ ቀናቶች ዉስጥ ስልክዎን ለማብራት እንዳይሞክሩ፡፡
6) ከጥቂት ቀናቶች በሗላ ስልክዎን ከሩዝ ዉስጥ ያዉጡ እና ባትሪዉን አስገብተዉ ያብሩት፡፡
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
ስልክዎ አሁንም ካልበራ ባትሪዉን ቻርጅ ያድርጉት፣ ቻርጅ ተደርጎም የማይበራ ከሆነ ባትሪዉ ብልሽት አጋጥሞታል ማለት ነዉ፡፡ ባትሪ ይቀይሩለት ወይም ወደ ስልክ ሰሪዎች ይዉሰዱት፡፡